የደቡብ ወሎ ዞን ገ/መምሪያ የመኪና እቃዎች እና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደወገ/መ/ግቡ/ግጨ1/002/2014
የደቡብ ወሎ ዞን ገ/መምሪያ ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎችና ተጠሪ ጽ/ቤቶች ለ2015 በጀት ዓመት መምሪያው
- በሎት 1 የመኪና እቃዎች እና
- በሎት 2. የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
በመሆኑም፤
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin ያላቸው፣
- የግዥ መጠኑ 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ VAT የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ኦሪጅናል ዕቃ መሙላት እና ያሽነፉባቸውን ዕቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው።
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሣ ብር) በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒው ከኦሪጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ ኣለበት።
- አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያሲዝ ይሆናል።
- ውድድሩ የሚካሄደው የመኪና እቃዎቹ በመኪና ሞዴል በሎት ድምር ሲሆን የመኪና ጎማው አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ውድድር ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ገመምሪያ በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡oo ሰዓት ይታሸጋል፤ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ሰዓት ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 81 18 /19 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ድርጅት ተጫራች ኦሪጅናል ዕቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። እንዲሁም በየፑሉ በሚገኘው ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
የደቡብ ወሎ ዞን ገ/መምሪያ የግዥና/ን/አስ
