በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ በለሳ ወ/ገ/ጽ/ቤት/ በወረዳው ስር ላሉ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዉል በመስጠት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ በለሳ ወ/ገ/ጽ/ቤት/ በወረዳው ስር ላሉ መኪና ላላቸዉ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል አመታዊ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም የሚቆይ በመደበኛ በጀት
በበኩር ጋዜጣ በወጣዉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዉል በመስጠት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም መወዳደር ለምትፈልጉ ድርጅቶች በሙሉ የጨረታ ሰነዱን በምስ/በለሳ ወ/ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 16
በመቅረብ የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) ብር በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ለመጫረት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርትፍኬት \ቲን \ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /200 ሺህ/ እና ከዚያ በላይ የሆነ።
3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
4. ተጫራቾች በጨረታው የሚገቡትን ውለታ በአግባቡ የሚፈጽሙ መሆን አለባቸው።
5. ማንኛውም ተጫራች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም።
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶችን በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታዉ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
7. ጨረታው ለ15 ቀን አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኘበት 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ላይ ጀምሮ በይፋ ይከፈታል።
8. የታዘዘው የመኪና እቃ በበጀት እጥረት ምክንያት አንሶ ሳይገዛ ቢቀር ፅ/ቤቱ የማይገደድ መሆኑን እንገልጸለን።
9. መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን የበዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
11. ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅሬታ ማስተናገድ የምንችል መሆኑን እንገልፃለን።
12. የጨሪታው አሸናፊ የሚለየው ጥቅል በሞሉት ዝቅተኛ ድምር ዋጋ ነው።
13. ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ ምስ/በ/ወ/ግ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0583390004/0116 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
14. ድርጅቱ ጨረታዉ ሲከፈት ለማገናዘብ ኦርጅናል መረጃዉን ማቅረብና ከፖስታዉ ላይ ማህተሙን፣ ስም እና ፊርማዉን ማስቀመጥ አለበት።
15. የሚገዙት /የሚቀርበዉ የመኪና እቃዎች መለዋወጫዎች/ አሸናፊዉ ድርጅት እስከ ጎንደር ከተማ ጋራጅ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
ማሳሰቢያ ፡- የሚቀርቡት እቃዎች በእስፔስፊኬሽኑ መሰረት ኦርጅናል መሆን አለባቸዉ። አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፋቸዉን እቃዎች ጽ/ቤታችን በሚፈልግበት ጊዜና ቦታ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወዲያዉኑ ማቅረብ
የሚችል መሆን አለበት።
የምስራቅ በለሳ /ወ/ገ/ጽ/ቤት
