Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Jul 2022, 1:57 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የመርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሰብል አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሰብል ሽያጭ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.የሰብል በቆሎ ሽያጭ አምስት ሺህ /5000/ ኩ/ል ባህርዳር ከተማ መጋዝን፣ አምስት ሺህ/5000/ኩ/ል ዱርቤቴ ከተማ መጋዝን፣ አምስት ሺህ /5000/ ኩ/ል ሰ/ሜጫ ወረዳ ወተት አባይ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ መጋዝን እና ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ /2150.00/ ኩ/ል ደ/አቸፈር ወረዳ ቀልጣፋ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማህበር አሁሪ ቅርጫፍ መጋዝን በድምሩ አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ /17150.00/ ኩ/ል በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1.  በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2.  በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3.  ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  4.  ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  5. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 300 ብር የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይቻላል፡፡
  6.  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00  ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  7. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ንግድ ፍቃዱ ላይ የተቀመጠው የስራ አስኪያጅ ስም እና ቅጹ የሞላው ሰው ስም አንድ አይነት መሆን አለበት፡፡ ተወካይ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ ማያያዝ አለበት፡፡
  8. ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡30 ለዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9.  የጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡ይህ ማድረግ ካልቻለ የጨረታ ማስከበሪያው ይወርሳል፡፡
  11. የሚሸጠው መጠን በ20 በመቶ ሊቀንስም ወይም ሊጨምርም ይችላል፣ አሽናፊው የሚለየው በየሎቱ ይሆናል፡፡
  12. አሽናፊው የአሽነፈውን ሰብል በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ሊያነሳ የሚወስድ ነው፣ አሸናፊው የአሸነፈውን ሰብል ለፍትህ ለውል ምርመራ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል/ይሸፍናል፡፡
  13.  በየሎቱ ለይቶ መሙላት ይቻላል እንዲሁም ሁሉንም ሎት መሙላት ይቻላል፡፡ ከአንድ ሎቱ ውስጥ ግን ቀንሶ መሙላት አይቻልም፡፡
  14. ሰብሉ የሚገኝበት ቦታ በባህርዳር ከተማ፣ ዱርቤቴ ከተማ፣ ሰ/ሜጫ ወረዳ ወተት አባይ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ(ቢኮሎ ከተማ) እና ደ/አቸፈር ወረዳ ቀልጣፋ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ አሁሪ ቅርጫፍ ሲሆን ጥራቱን በአካል በማየት
    መሙላት ይቻላል፡፡
  15.  አሽናፊው የወዛደር የማስጫኛ እና የትራንስፖርት ውጪ እራሱ አሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  16. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨርታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 55/2012 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 0918341125/0911590534 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የመርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.

Save Tender