በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ግልጽ የደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ እነገት ቀበሌ ልዩ ስሙ ሟርተኝ ከተባለ ቦታ የለማ የአዲስ አንባ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ደን
1. የፈረንጅ ፅድ እና 2.ዲከረንስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
-ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆነን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጎዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላቸው፣
- የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስርጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- . የሚሸጡ ደኖችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ እና የሚሸጡ ችግኞች የመሸጫ መነሻ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የአካባቢና ደን ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ከማስገባታቸው በፊት ለጨረታ ሰነዱ ግዥ የማይመለስ ብር 150/ አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ
ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ - ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት
ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት ማስባት ይኖርባቸዋል፡፡ - ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የአካባቢና ደን ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4:00 ላይ ይከፈታል፡፡
- ሰበካ ጉባኤው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ያወጡትን ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡
- አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈውን የዲከረንስ ደን ወረዳው ድረስ በመምጣት በራሱ ትራንስፖርትና ማንኛውም ወጭ በራሱ ሸፍኖ መውሰድ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ሰበካ ጉባኤው የጨረታ አሸናፊውን በነጠላ ዋጋ ይለያል፡፡
- ተጫረቾች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ አቤቱታ ወይም ቅሬታ ካላቸው በተከታታይ 5 የስራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ደኑ ማለትም የፈረንጅ ፅድ እና ዲከረንሱን ከቦታው ድረስ በመግባት የምናስረክብ ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን ጽ/ቤቱ ይገልጻል፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ሮያሊቲ 13 በመቶ እና ሌሎች ክፍያዎችን በቅድሚያ ለሚመለከተው አካል መክፈል የሚችል መሆን እንዳለበት እንገልጻለን፡፡
- ሽያጭ ፈጻሚው አካል ሸያጩን ለመገምገም ለማፅደቅ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና ከአሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስከሚፀና ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ፀንቶ የሚቆይበት ለ40 ቀን ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0910050544/0910064469 በመደወል ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የአዲስ አንባ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
