የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የተለያዩ የሚኪና ጐማዎች እና ኢሮ ኬብል ፓናል ቦርድ/ስዊች ቦርድ/በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የተለያዩ የሚኪና ጐማዎች እና ኢሮ ኬብል ፓናል ቦርድ/ስዎች ቦርድ/በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡
- ሎት(ምድብ)1 የተለያዩ የመኪና ጐማዎች
- ሎት(ምድብ)2 ኢሮ ኬብል (Euro cable) እና
- ሎት(ምድብ)3 control panel board /swich board/ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ /የታደሰ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 200-20 የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናሉን፣ ኮፒውን እና ሲፒኦ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 200-02 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/un Conditional Bank Garanty / ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 200-02 ቴክኒክ ሰነዱ ብቻ ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም የተለያዩ የመኪና ጐማዎች የተለያየ ኢሮ ኬብል እና ፓናል ቦርድ /ስዊች ቦርድ/ ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058-320-50-79 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የባህር ዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
