Tender Detail

Tender Details

  • Deadline03 Sep 2022, 11:31 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Spare Parts

የፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ የመኪና ጐማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ የመኪና ጐማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በዚህ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የጨረታ ሰነዱ መሸጫ ብር 50 (ሀምሳ ብር) ሲሆን በኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝርና መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ 10,000/አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት አለባቸው።
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ3፡30 ይከፈታል። ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም።
  10. ተጫራቾች ሞልተው በሚያቀርቡት ሰነድ የባለቤትነት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን ፊርማና ማህተም ያለበት መሆን አለበት።
  11. ተጫራቾች ተወዳድረው የሚያሸንፏቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ሙሉ ወጪ ፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ገቢ ያደርጋሉ። እንዲሁም መስሪያ ቤቱ 20 በመቶ የመቀነስ የመጨመር መብት አለው።
  12. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ ውል ማስከበሪያ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ማስያዝ ይኖርበታል።
  13. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ።
  14.  አሸናፊ የሚመረጠው ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ በተያያዘው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መግለጫና በሚቀርበው ዝቅተኛ ዋጋ ሆኖ መስሪያ ቤቱን በሚጠቅም መሰረት ይሆናል።
  15.  መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት ወይም በ 058 775 0254 /058 775 1270 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

የፍኖተ ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ

Save Tender