አዲስ አምባ የተቀናጀ የበጎ አድራጎት ድርጅት የ2014 ሂሣብ ዓመት የሂሣብ መዝገቡን በውጭ ኦዲተር አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አምባ የተቀናጀ የበጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማህበረሠብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 መሠረት የተቋቋመ አገር በቀል የሲቪል ማህበራት ድርጅት ሲሆን የ2014 ሂሣብ አመት የሂሣብ መዝገቡን በውጭ ኦዲተር አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
1. በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና አዲት ቦርድ ወይም እርሱ በወከለው ህጋዊአካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለው የሙያ ፈቃድ ያለው እና ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
2. የኦዲት ስራ ለመስራት የሚያስችል ለ2014 የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያለው
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና የምስክር ወረቀቱን ማቅረብ የሚችል
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ያለው
5. ከዚህ በፊት የኦዲት አገልግሎት ከሰጠባቸው ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈፃጸም የምስክር ወረቀት የምስጋና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛላችሁን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት የስራ ቀኖች በማህበሩ የኢሜል አድራሻ addisamba30@gmail.com በመላክ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሣውቃለን።
- ስልክ 0940 80 25 39/0922 69 36 17
አዲስ አምባ የተቀናጀ የበጎ አድራጎት ድርጅት
