በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. 24,000 (ሃያ አራት ሺህ) ኩ/ል ነጭ በቆሎ ቡሬ ከተማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የሰብል ሽያጭ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕ/ጐ/ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ. 24,000 (ሃያ አራት ሽህ) ኩ/ል ነጭ በቆሎ ቡሬ ከተማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል ፡፡
ስለሆነም፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ሲሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፓስታ ውስጥ በማስገባት ማስያዝ አለበት፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 100 (አንድ ብር) የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 11የስራ ቀናት አየር ላይ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዳችው ዪኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በ11ኛው ቀን 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
- ጨረታውን ያሽነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፈቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው 2 በመቶ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ (ተወካይ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ ማያያዝ አለበት)፡፡
- አሸናፊው ሰብሉን አንስቶ የሚጨርስበት 45 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
- የማስጫኛ እና ሌሎች ወጭዎችን ገዥ የሚሽፍን ይሆናል፡፡
- ተጫራቶች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 0640/1032በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ.
