የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ለረጅም ጊዜ የተጠራቀመ የHDPE pipe Scrap እና Geomembrane Scrap ፈጭቶ ለፔሌታይዘንግ ስራ ያዘጋጀው ሲሆን ይህን የተፈጨ ስክራፕ ፔሌታይዝ (ወደ ጥሬ እቃ) መቀየር (Recycle) ማድረግ የሚችሉ ድርጅቶችን በማወዳደር የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይህን ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አውጥቷል
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር APF/02/2015/Local
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኝ ሲሆን በፋብሪካው ግቢ ውስጥ ያለውን ለረጅም ጊዜ የተጠራቀመ የHDPE pipe Scrap እና Geomembrane Scrap ፈጭቶ ለፔሌታይዘንግ ስራ ያዘጋጀው ሲሆን ይህን የተፈጨ ስክራፕ ፔሌታይዝ (ወደ ጥሬ እቃ) መቀየር (Recycle) ማድረግ የሚችሉ ድርጅቶችን በማወዳደር የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ይህን ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
አውጥቷል፡፡
የአገልግሎት የጊዜ ገደቡ በማሽኖች የማምረት አቅም የሚወሰን ቢሆንም ካለው የረጅም ጊዜ ክምችት አኳያ ሲታይ በትንሹ 6 ተከታታይ ወራት እና ከዚያ በላይ የሚፈጅ ይሆናል፡፡
ሀ. ከተጫራች ድርጅቶች መቅረብ ያለባቸው የውድድር ቅድመ መስፈርቶች
- ተጫራቾች ለውድድር በሚያቀርቡት ማሽን የተመረተ ግብአት (ፔሌታይዝድ የተደረገ Recycle ጥሬ እቃ) ቢያንስ አንድ ኪ.ግ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተወዳዳሪ ማሽኑን በራሱ ወጪ በማጓጓዝ በፋብሪካው ግቢ ውስጥ በተፈቀደለት ቦታ የመትከል ኃላፊነት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ለስራው ያቀረበውን ማሽን የማምረት አቅም (kg/h) እና የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ (kwh) የሚያሳይ ማንዋል የማቅረብ ወይም በደብዳቤ ማረጋገጫ የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ለስራው የሚያሰማራቸውን ሰራተኞች የማጓጓዝ እና የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ፔሌታይዝ ያደረገውን ጥሬ እቃ ርክክብ እስከ ሚደረግ ድረስ በአግባቡ በንፅህና የመጠበቅ እና በርክክብ ወቅት መዝኖ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
ለ. በፋብሪካው በኩል የሚቀርቡ መሠረተ ልማቶች እና ሌሎች አቅርቦቶች
ለማሽን መትከያ ቦታ ማዘጋጀት
የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ እና የኃይል አቅርቦት
የውሃ እና የንፋስ መስመር ዝርጋታ እና አቅርቦት
Recycle የሚደረግ የተፈጨ ስክራፕ በኪሎ ግራም የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
1. ለስራው የሚያቀርቡትን ማሽን የባለቤትነት ማረጋገጫ የሚያሳይ ወይም የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ለ2014 በጀት ዓመት የታደሰ የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሠነዶችን ማለትም የንግድ ስራ ፈቃድ፡የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፡ የግብር ከፋይነት /ቲን/ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ማቅረብ
አለባቸዉ፡፡
3. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 103 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ
ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 ላይ የተገለፀዉ ቢኖርም በአካል በመገኘት ሠነዱን መግዛት የማይችሉ ተጫራቾች በአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ቅርንጫፍ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር
1000013149996 ገንዘቡን ብር 300(ሦስት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኙን በኢ-ሜይል አድራሻችን amharapipefactory@gmail.com በመላክ የጨረታ ሠነዱን ሶፍት ኮፒ በe-mail በማግኘት
በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
5. ተወዳዳሪ ድርጅቶች ያቀረቡትን የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፋብሪካው ስም
በማሰራት የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለበት፡፡
6. የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታዉ አየር ላይ በዋለበት በ16ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ይከፈታል፡፡
8. 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይሆናል፡፡
9. በውድድሩ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን አሸናፊው ተወዳዳሪ የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጨምሮ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማቅረብ የአቅርቦት ውል
የሚፈፀም ይሆናል፡፡
10. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 206 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09-35-98-37-29 መደወል ይችላሉ፡፡
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ
