የመንዝ እና ግሼ ልማት ማህበር የ2014 ዓ.ም. የስራ ዘመን የሂሳብ እንቅስቃሴው በሙሉ በግልጽ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንዝ እና ግሼ ልማት ማህበር በሰርተፍኬት ቁጥር 5603 ሀገር በቀል የበጎ አድራት ድርጅት ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ፍቃድ አግኝቷል። የማህበሩ የ2014 ዓ.ም. የስራ ዘመን የሂሳብ እንቅስቃሴው በሙሉ በግልጽ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው እንድትወዳደሩ እንጠይቃለን።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸው።
- የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- ስራውን ሙያው በሚጠይቀው ስታንዳርድ እና ጥራት በ1ወር ጊዜ ውስጥ ሰርተው ማጠናቀቅ።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
ማሳሰቢያ፦
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት በማህበሩ ቢሮ በመገኘት የስራውን ስፋት እና የዶክመንት ብዛት በማየት የስራውን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ማህበሩ ቢሮ ማስገባት ትችላላችሁ።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ ስሙን ፊርማን አድራሻውን ማህተሙን በግልጽ ማድረግ ይኖርበታል።
- ከተጠቀሰው ጊዜ ውጭ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፦ መገናኛ ቢሊቪው ሆቴል ፊት ለፊት ያልው AB STAR ህንጻ 2ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 205
- ለበለጠ መረጃ 0919 22 90 92/011 683 4395/0985 85 44 54
የመንዝ እና ግሼ ልማት ማህበር
