በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው ብዛት 500 ኩንታል የዕጣን ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የዕጣን ምርቶች
ሽያጭ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-ኢምዘደውአዘ/ሸ02ለ/2014
በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና ደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ አዳማ እና ቻግኒ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚገኙ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው ብዛት 500 ኩንታል የዕጣን ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን:፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታhስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት (ከሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከ11፡00 ሰዓት በፊት) በዋናው መ/ቤት የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና ደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል የጨረታው ዋጋ ለ6o ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል የተለያየ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የዕጣን ምርቶች ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታከስ ይጨምራል።
- ጨረታው ሀምሌ 26 ቀን 2014 ዓም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ምርቶች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ 011 618 6125
ፋክስ 011 663 0892
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኢትጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፕሬሽን
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና ደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ
