Tender Detail

Tender Details

  • Deadline22 Jul 2022, 4:43 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printing And Publishing

የድሬድዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽ ጉዳዮች ቢሮ በ2015 በጀት አመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት የጋዜጣ ሕትመት አገልግሎት ለአስራ ሁለት ወር የሚቆይ ማዕቀፍ ውል ስምምነት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የጋዜጣ ህትመት ጨረታ ማስታወቂያ

የጨመ/ቁመኮ/01/2015

የድሬድዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽ ጉዳዮች ቢሮ በ2015 በጀት አመት ከመንግስት በተመደበለት በጀት የጋዜጣ ሕትመት አገልግሎት ለአስራ ሁለት ወር የሚቆይ ማዕቀፍ ውል ስምምነት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፦

  1. ተጫራቾች በህትመት ስራ የተሠማሩና የራሳቸው ማተሚያ ቤት ያላቸውና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና በመንግስት የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
  4. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን የህትመት አይነቶች ከዚህ በፊት በድርጅታቸው የሰሯቸውን ለሳምፕል ክጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ጨረታ አግባብነት ያለው የተሟላ ማስረጃና ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ  ጨረታው እስከሚታሸግበት እለትና ሰዓት ቀደም ብሎ የጨረታ ሰነዱን ከቢሮው የፋይናንስ ግዥና ንብረት ኦስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ቀርበው የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች አስፈላጊውን ዋጋ በግልጽ ማስገባት ይርቸዋል።
  7. የጨረታ ሳጥኑ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሸጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሥራ ሂደቱ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች ብር 10,000 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ በጥሬ ገንዘብ ዋስትና በባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም ከነዚህ አማራጮች በአንዱ በመጠቀም ለብቻው አንድ ፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

የድ/ዳ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

የስልክ ቁር 0252-11-60-62

ድሬዳዋ

Save Tender