የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ግንባታዎች ተሽከርካሪዎች የእርሻ መሣሪያዎች እና የመሬት ልማት በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
አንደኛ ደረጃ ዝግ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጌዲ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/ተየግ/ማህበር ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከተውን የእርሻ ልማት ፕሮጀክት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 98/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
የተበዳሪው/የመያዣ ሰጪው ስም |
ንብረት የሚገኝበት አድራሻ |
የሚሸጠው ንብረት ዓይነት
|
ጠቅላላ የመሬት ስፋት
|
የለማው መሬት መጠን
|
የሐራጁ መነሻ ዋጋ /ብር/
|
ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት
|
|
ጌዲ አግሮ ኢንዱስትሪ /የተ/የግ/ማህበር |
በጋንቤላ፣ ክልል እኝዋ ዞን ዲማ ወረዳ፣ ጌዱ ቀበሌ ውስጥ |
ግንባታዎች ተሽከርካሪዎች የእርሻ መሣሪያዎች እና የመሬት ልማት |
1017 ሄክታር
|
370.84 ሄክታር
|
11,923,014.60 (አሥራ አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ሦስት ሺህ አሥራ አራት ብር ከ60/100 ሣንቲም) |
06/1/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ
|
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (አንድ አራተኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ነሐሴ 05 ቀን 2014 ዓ.ም. ከ10፡00 (ሰዓት) ድረስ በጅማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል - በተጨማሪ ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ በሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠቃል።
- ሽያጩ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጅማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ውስጥ ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው በመገኘት ሂደቱን መከታተል ይችላሉ።
- አሸናፊው ተጫራች ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል።
- ገዢው ፕሮጀክቱን በገዛበት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው የጨረታ አሸናፊው ይከፍላል።
- የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች እና የእርሻ መሣሪያዎች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ከሆኑ ገዢው ቀረጥ ነፃ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግሥት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
- ባንኩ ለጨረታ የቀረበውን ንብረት የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ወይም አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና የፕሮጀክቱን ስራ የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።
- ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጅማ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 047-111-09-08 ወይም 047-111-0016 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።ፕሮጀክቶቹን መጐብኘት የሚፈልጉ ካሉ ከጅማ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መመልከት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሽያጩን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጅማ ዲስትሪክት
