Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Jul 2022, 3:52 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories General Service Provision

አቃቂ ቤዚክስ ሜታልስ ኢንዱስትሪ ለዋና መ/ቤትና በስሩ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት መግዛት ይፈልጋል


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በሦስተኛ ወገን የሚፈጸም የጥበቃ አገልግሎ ግዥ

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ግዥ

የጨረታ ቁጥር 008/2014

አቃቂ ቤዚክስ ሜታልስ ኢንዱስትሪ ለዋና መ/ቤትና በስሩ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት

  • ምድብ 1፡_ በተለያየ ክልል ከተሞች ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች፤
  • ምድብ 2፡_ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኘው ኢንዱስትሪ ለዋና መስሪያ ቤት የጥበቃ አገልገሎት ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. የ2013/2014 በጀት አመት ህጋዊና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የጊዜ ገደቡ ያላለፈበት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከሚመለከተው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (Tax Clearance) የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀቅ (VAT)፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ በአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (PPA Website supplier list) ማቅረብ አለባቸው
  2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አቃቂ ቤዚክስ ሜታልስ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር እየከፈሉ ደረሰኝ በማቅረብ ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 41 በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ጨረታው ባለ ሁለት ፖስታ በመሆኑ ሰነዳቸውን (የዋጋ እና የቴክኒካል) በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከኦርጅናሉ በተጨማሪ ሁለት ቅጂ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ መሆኑን በፖስታ ላይ በግልጽ በመጻፍ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 41 በመምጣት እንድታስገቡ።
  4. የጨረታ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛው ቀን ከረፉዱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመሰብሰቢያ አደራሽ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፡ ለምድብ 1፡ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር) በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ ለምድብ 2፡ ብር 40,000.00 (አርባ ሺ ብር) በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በቴክኒካል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
  7. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ- ከአ/አ ወደ ደ/ዘይት መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ገላን ከተማ ሳይደርስ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከ ASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

ለተጨማሪ መረጃ - ስልክ ቁጥር 011 434 0409/011 435 0608

ሞባይል ቁጥር 0924 34 87 39/0911 86 75 50

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ

Save Tender