Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Aug 2022, 2:32 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ጸሐይ በቀለ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ሀየሉ ጀምበሬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 173072 በ23/2/2014 ዓ.ም እና በመ/ቁ 162194 በ17/10/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የቤቁ 046 ቤት ውስጥ ከዋናው ቤትና ከዋናው ቤት ፊት ለፊት የተሰራ ቤት ውጭ ያለ ከዋናው ቤት ውጭ ያለው ቤት ከዋናው ያረፈበት 67 ካ.ሜትር በስተጀርባ ያሉ ሁሉም ሰርቢስ ቤቶች የውርስ ሀብት በመሆናቸው ቤቱ የቦታ ስፋት በካርታ ላይ በተመለከተ ካርታው በፕሮፖርሽን (በተነፃፃሪ) የተሰጠ ሲሆን ጠቅላላ ስፋቱ 90 ካሜትር ሲሆን የሚደርሰው 350 ካ/ሜትር ሆኑን ነገር ግን ይሄ ከላይ የተጠቀሱት የቦታ ስፋቶች በአጠቃላይ ቤት ቁጥር 046 መሆኑ እንዲታወቅ ከቤት ቁጥር 046 ውስጥ የሚገባው (የማይሸጥ) መሆኑ እንዲታወቅ የቤ/ቁጥር 046 ውስጥ ደግሞ ዋና ቤትና ከዋናው ቤት ፊት ለፊት ያለው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 283,880,000 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሶስት ሺ ስምንት መቶ ሰማኒያ ብር ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 5 ቀን 2014 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል።የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።

በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender