Tender Detail

Tender Details

  • Deadline29 Jul 2022, 1:14 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Generators

የጄኔሬተር ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አቶ ብርሃኑ አለሙ እና በፍ/ባለዕዳ አፍሮ ፂዮን ኮንስትራክሽን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/269207 273531 በሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ/ም እና በ21/04/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ  ከተማ ወረዳ 4 በፍ/ባለዕዳ ግቢ የሚገኝ ጄኔሬተር የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 9:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬhቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬhቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንከ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬከቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በኢ.ፌዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዲራል ፍ/ቤቶች

ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

Save Tender