አዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጸውን ለተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የጨረታው ዓይነትና
|
የጨረታ መለያ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ምርመራ |
|
1 |
የባልትና ውጤቶች አቅርቦት ግዥ : -በርበሬ ፣ ሽሮና እርድ |
አአሳቴዩ/ግጨ/ዕግ/007/2015
|
40,000.00 (አርባ ሺህ ብር)
|
|
|
2 |
የምግብ ምርቶች አቅርቦት ግዥ፡-ሳልሳ ፣ ጨው ፣አትክልት ቅቤ ፣ ሻይ ቅጠልና ሩዝ |
አአሳቴዩ/ግጨ/ዕግ/006/2015
|
40,000.00 (አርባ ሺህ ብር)
|
|
|
3 |
የማገዶ እንጨት አቅርቦት ግዥ |
አአሳቴዩ/ግጨ/ዕግ/003/2015
|
6,500.00 (ስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር) |
|
|
4 |
የፍራፍሬና አትክልት አቅርቦት ግዥ፡- ብርቱካን ፣ ቀይ ሽንኩርት ፣ ጥቅል ጎመን ፣ ቃሪያ ፣ ድንች ፣ካሮት ፣ ቲማቲም ፣ዝንጅብልና ነጭ ሽንኩርት |
አአሳቴዩ/ግጨ/ዕግ/006/2015
|
60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር)
|
|
በመሆኑም ተጫራቾች፤
- 2014/2015 ዓ.ም ህጋዊ በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የጊዜ ገደቡ ያላለፈበት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከሚመለከተው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (Tax Clearance) ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት(VAT)፣በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገጽ በእቃ/አገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (Website supplier list) ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ለእያንዳንዱ ምድብ በአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000007971544 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እየከፈሉ ደረሰኝ በማቅረብ ከታች በተገለጸው አድራሻ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 62 1ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 116/103 ዘወትር በመንግስት ሥራ ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ባለ አንድ ፖስታ በመሆኑ 1(አንድ) ኦርጅናል የቴክኒካልና የዋጋ ፕሮፖዛል እና 2(ሁለት) የዋናው ሰነድ ኮፒ ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ በድምሩ 3 (ሶስት) ፖስታ ለየምድቡ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ኦርጂናል እና ኮፒ በሚል እንዲሁም የምድቡ ስም በፖስታው ላይ በግልጽ በመጻፍ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከታች በተመለከተው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከረፉዱ 4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ 4:30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ህንፃ ቁጥር 62 የጨረታ መክፈቻ ምድር ወለል ላይ በሚገኘው አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ብር ከላይ በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ በሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ኦርጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ወይም ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ-በአቃቂ ቃሊቲ መስመር ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ወደ ኮዬ ፈጬ አደባባይ በሚወስደው መንገድ ወይም በጎሮ መስመር ቱሊዲምቱ አደባባይ ሳይደርስ በስተቀኝ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር፡0118960787
የአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
