የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጫማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU-AEU/NCB/039/2014
የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተገለፀውን ጫማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
መለኪያ |
የእቃው ብዛት |
|
1 |
ፕላስቲክ ቦት ጫማ |
በቁጥር |
500 |
|
2 |
የወንድ ቆዳ ስፔሻል ሴፍቲ ጫማ /ሄቪ ዲዩቲ/ |
በቁጥር |
3000 |
በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሠነዱን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት ቀበሌ 16 ኖክ ነዳጅ ማደያ ወይም ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት ሀቂቃ የገበያ ማዕከል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.015 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡:
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እስከ ሀምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በተራ ቁጥር 2 በተገለፀው አድራሻ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ሀምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል።
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582207469/0583201957 መጠየቅ ይችላሉ።
የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት
