Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Jul 2022, 12:04 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Agriculture And Farming

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ጥሬ ዕቃዎች ፣ ሸቀጣሸቀጥ ፣ የቁም ከብት እና የማገዶ እንጨት አቅርቦት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር OBU-ONT-01-2015

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ጥሬ ዕቃዎች ፣ ሸቀጣሸቀጥ ፣ የቁም ከብት እና የማገዶ እንጨት አቅርቦት አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊ ብቃት ያላቸውን የአገር ውስጥ ተጫራቾች ይጋብዛል።

በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ

1. የጨረታ ሰነዱን ከታች ከተጠቀሱት አድራሻዎች የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

2. የጨረታ ሰነዶቻቸው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ግዢ ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3.የጨረታ ሳጥን በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ግዢ ክፍል ይከፈታል።

4.1. በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ለመታደሱ ማረጋገጫ

4.2. ማንኛውንም የወቅቱን የመንግሥት ገቢ ግብር ለመክፈላቸው ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋገጫ

4.3 በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል

4.4 ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል

4.5 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.6 ከኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢና ጥራት ኤጀንሲ የተሰጠ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ግዥ ማስረከቢያ ቦታ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግብ መሆኑን ማወቅ አለባቸው

6. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የስራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ የጫኝና አውራጅ አካተው ማቅረብ አለባቸው።

9. ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መጠየቅ ይችላሉ።

ስልክ ቁጥር 025 551 0878/1606/1610

ፋክስ ቁጥር 025 551 0182

 

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ

Company Info
Save Tender