Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Jul 2022, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Agriculture And Farming

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎች እና አገልግሎት ለአንድ ዓመት በማዕቀፍ ስምምነት የሚሆን ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BHU 01/2015

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተጠቀሱ ሎት ያሉ ዕቃዎች እና አገልግሎት ለአንድ ዓመት በማዕቀፍ ስምምነት የሚሆን ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1፡- የባልትና ውጤቶች አቅርቦት
  • ሎት 2:- የዳቦ አቅርቦት
  • ሎት 3፡- የአትክልት አቅርቦት
  • ሎት 4:- የፋብሪካ ውጤቶች አቅርቦት
  • ሎት 5:- የማገዶ እንጨት አቅርቦት
  • ሎት 6፡- የጤፍ አቅርቦት
  • ሎት 7፡- የሥጋ አቅርቦት

ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መዳደር ይችላሉ

  1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ንግድ መስክ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃዳቸውን፣ ዓመታዊ የሥራ ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው እና በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የመረጃ ሰነዶቻቸውን ኮፒ ከመጫረቻ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት ለሎት 1 ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር/፣ ለሎት 2 ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/፣ ለሎት 3 ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/፣ ለሎት 4 ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/፣ ለሎት 5 ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/፣ ለሎት 6 ብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር/ እና ለሎት 7 ብር 150,000 ( አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ስም በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንት ቢያንስ 120 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
  3.  ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስት ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግዥ አስተዳር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት ሎት የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በሚል ተጽፎ በተናጠል ፖስታ በማድረግ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተገለጸው መሠረት ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ቦታ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. የጨረታው ሳጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ እና የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣይ የሥራ ቀን ይተላለፋል።
  6. በሎት 2 የዳቦ አቅርቦት ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ዘመናዊ እና ማንዋል የዳቦ መጋገሪያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በተጨማሪም ለዳቦ ማመላለሻ ብቻ የሚሆን ሽፋን መኪና ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ አድርጎ ክፍያውን ይቀበላል፡፡
  9. ጨረታው በመንግስት የግዥ መመሪያ፤ ህግ እና ደንብ መሰረት የሚመራ ይሆናል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 046 443 0174/062 ፋክስ፡- 046 443 0355/352

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

Company Info
Save Tender