ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የፊልድ መኪና ፣ የጭነት የውሃ ማመላለሻ ቦቴ እንዲሁም የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መኪና አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የፊልድ መኪና ፣ የጭነት የውሃ ማመላለሻ ቦቴ እንዲሁም የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መኪና አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ሕጋዊ ብቃት ያላቸው የአገር ውስጥ ተጫራቾች ይጋብዛል፡፡
በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ
1. የጨረታ ሰነዱን ከታች ከተጠቀሱት አድራሻዎች የማይመለስ ብር 150 / አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሐምሌ 6/ 2014 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሣጥን ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ግዢ ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3. የጨረታ ሳጥን በዚሁ ዕለት ከቀኑ 5:15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ግዢ ክፍል ይከፈታል፡፡
4.1 በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ለመታደሱ ማረጋገጫ፡
4.2 ማንኛውም የወቅቱን የመንግሥት ገቢ ግብር ለመክፈላቸው ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋገጫ
4.3 በመንግሥት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4.5 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00/ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4.6 ከኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢና ጥራት ኤጀንሲ የተሰጠ ሠርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ግዥ ማስረከቢያ ቦታ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
6. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ካሻነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የሥራ አፈጻጸም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆኑ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ተጫራቾች ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ የጫኝና አውራጅ አካተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻቸው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ኦዶ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ
ስልክ ቁጥር 025 551 0878/1606/1610
ፋክስ ቁጥር በ2565101610
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ
ጭሮ
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት አዲስ አበባ
አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ አጠገብ የድሮ ጀርመን ካልቸራል
ኢንስቲትዩት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15
ስልክ ቁጥር 011 157 1847/011 157 1216
ፋክስ ቁጥር 011 157 1266 አዲስ አበባ
