Tender Detail

Tender Details

  • Deadline28 Sep 2022, 10:32 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Advertising And Promotion

የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ።


የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁ 1238/2013 አንቀጽ 30 በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ለማቋቋም የሚፈልጉ አመልካቾችን አወዳድሮ ለ5 አመልካቾች ፈቃድ መስጠት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት፡-

  1. ፈቃድ ለመስጠት የታሰበው ብሮድካስት አገልግሎት ዓይነት- የኤፍ ኤም ሬዲዮ፣
  2. አገልግሎቱ የሚሸፍነው አካባቢ፡- አዲስ አበባ፣
  3. ዝግጁ የሆኑት የሬዲዮ ሞገዶች- 92.5፣ 93.5፣ 94.5፣ 95.5 እና 96.5 (MHZ) ናቸው
  4. የፈቃድ ሁኔታዎችና ግዴታዎች ማኛውም ባለፈቃድ ፈቃዱን ለመውሲድ ባመለከተበት ወቅት በማመልከቻው የለጻቸው እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 እና አዋጁን ተከትለው በሚወጡ ደንብና መመሪያዎች መሰረት በፈቃዱ ውስጥ የተመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች የፈቃዱ ግዴታዎች ሆነው ይቆጠራሉ
  5. የማመልከቻ ማቅረቢያ ጊዜና ቦታ፡በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት የ3 ወር ጊዜ ውስጥ ከኤግዚቢሽን ማዕከል ጀርባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የፋይናንስ፣ ግዥ፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ማስተባበሪያ ቢሮ ቁጥር 101 ብር 50 (ሃምሣ ብር) (መከፈል የማልከቻ ቅጽ ወስዳችሁ በመሙላት እና ለውድድሩ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ከማመልከቻ ቅጹ ጋር በማያያዝ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ተጫራቾች የፕሮጀክት ሰነዳቸውን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 3 ወር ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡
  6. የብሮድካስት ፈቃዱ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 6 ዓመት ሲሆን የፈቃድ ዘመኑ ሲጠናቀቅ የሚታደስ ይሆናል፡፡
  7. የማመልከቻና የፈቃድ ክፍያ መጠን፤- አመልካቹ ፈቃድ እንዲሰጠው ሲወሰን የማመልከቻ ብር 500 እና የፈቃድ ብር 75,000 (በድምሩ ሰባ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ይከፍላል፡፡
  8. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በታተመ በ91ኛው ዕለት በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል::
  9. ባለሥልጣኑ ጨረታውን የመሰረዝ ሙብቱ የተጠበቀ ነው 

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 553 8755/56/65/66 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን

Save Tender