Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Jul 2022, 9:55 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Consultancy Service

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ በጅማ ዞን በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች (መና ፣ ሰቃ-ጮቆርሳ ና ጎማ ወረዳዎች) የቡና አገልግሎት ህብረት ሥራ ማህበራትና ዩኔን Cooperative Profile Development for Marketing Support ለማሰራት ይፈልጋል።


የኮንሰልታንሲ ሥራ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ደቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ በጅማ ዞን በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች (መና፣ ሰቃ-ጮቆርሳ ና ጎማ ወረዳዎች) የቡና አገልግሎት ህብረት ሥራ ማህበራትና ዩኔን Cooperative Profile Development for marketing support  ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም የታደሰና ህጋዊ የኮንሰልታንሲ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ ህጋዊ የሆነ ደረሰኝ ና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን 200 ብር በመክፈል ከድርጅቱ መግዛት የሚችሉ ሰሆን፤ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2/በመቶ በሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ደቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ9 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ መስቀል ፍላዎር አደባባይ አከባቢ በሚገኘው ቪላ ቨርዴ ሆቴል አጠገብ ባለው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ማቅረብ ይችላሉ።

መወዳደሪያ ሰነዱን ማስገባት የሚቻለው በ አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ሲሆን በአስራ አምስተኛው ቀን ግን እስከ ረፋዱ 5፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን ከረፋዱ በ5፡01 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ በ5፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

ተጫራቾች የስራውን Terms of Reference (ToR) ከድርጅቱ ማገኘት ይችላሉ።ማሳሰቢያ፡– ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ  የኮንሰልታንሲ ሥራውን   በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡–

 

አዲስ አበባ፡ መስቀል ፍላወር አካባቢ፣ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን ጀርባ፣ ከቪላ ቨርዴ ሆቴል ገባ ብሎ፤ St. No 3-553d, B15-8፤ ስልክ ቁጥር፡/011 558 3967፣ 091 168 0901፣ 091 182 2126

Save Tender