የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ትራክተር እና ማረሻ በሐራጅ መሸጥ ወይም ማከራየት ይፈልጋል።
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የማሽነሪ እቃዎች በኪራይ ወስዶ የነበረና ከዚህ በታች ስሙ የተጠቀሰው ተከራይ ከባንኩ ጋር በተዋዋለው የካፒታል እቃ ዱቤ ግዥ እና ኪራይ ውል ስምምነት መሠረት የሊዝ ኪራይ ክፍያቸውን ተመላሽ ባለማድረጉ ምክንያት ከዚህ በታች የተመለከተውን ባንኩ ከደንበኛው መልሶ የተረከበውን ማሽነሪዎች እና እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ወይም ማከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተከራይ ስም |
በጨረታ የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ |
የንብረቱ ዝርዝርና ዓይነት
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
የጨረታ ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
ቢ.ኤል.ኤም.ኤም የተቀናጀ እርሻ ልማት ድርጅት |
በባንኩ አዳማ ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ የሚገኝ |
1ትራክተር (Massey Ferguson, 120hp) ማረሻ Nardi Disc plough,4 disc) |
1,640,500.00
|
ዝግ ጨረታ |
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ዳሽን ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 307 ላይ ሀምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡oo ሰዓት
|
የጨረታ መመሪያ፦
- ንብረቱን መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ የጨረታን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የሐራጅ ጨረታው በሚከናወንበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የተጠቀሰውን ንብረት መግዛት የሚፈልግ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሀምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ድረስ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ዳሽን ባንክ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ማስገባት አለበት፤
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ሀምሌ 06/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፤
- በጨረታ ለተሸነፉት ተሳታፊዎች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፣
- ንብረቱን በከፈል መከራየት የሚፈልግ ተጫራች የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት ማሟላትና ቢያንስ 1/4ኛ ቅድሚያ ያሸነፈበት ዋጋ መክፈል ግዴታ ይኖርበታል፣
- ተጫራቹ በጥሬ ገንዘብ አሸናፊ ከሆነ ቀሪውን ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ የጨረታው አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣
- ተጫራቹ በከፊል ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ከፍያ አጠቃሎ በመከፈል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታው አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣
- 15% የተጨማሪ እሴት ታhስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
- ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት ዳሽን ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 307 በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡-022-211-5329/022-212–0357/ 0910–41-13-69 ላይ መደወል ይቻላል፡፡አስቀድመው ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልጉ ካሉ ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ፤
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት
