የጫማ መሳሪያ ማሽኖች የሐራጅ ሽያጭ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ ወንድሙ ኩመላ እና በፍ/ባለዕዳ ሲ ደብሊው ሲ (CWC) ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/100389 በ4/05/14 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/101263 በ24/9/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር አዲስ በሆነው ቤት ውስጥ የሚገኙበት የጫማ መሳሪያ ማሽኖች የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 2,699,000 (ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ብር) መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 25/2014 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 9፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ንብረትነቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታhስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬከቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
