በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰሜን ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ፍ/ቤት የመኖሪያ ቤትና ቦታ የሐራጅ ሽያጭ።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በአፈ.ከሳሽ ሀይለማርያም ወልደስላሴ እና በአፈ.ተከሳሽ ወ/ሮ እታለም ታደሰ መካከል ስላለው የአፈፃጸም ክስ ጉዳይ በግራ ቀኙ ተከራካሪዎች ስም ተመዝግቦ የሚገኘው በሞላሌ ከተማ 01 ቀበሌ ዞን 3 አዋሳኙ ከምስራቅ መንገድ ከምዕራብ የሟች ተስፋዬ ግዛቸው ከሰሜን የሽጥላ ገ/ወልድ ከደቡብ የገዘሀኝ ላቀው መካከል የሚገኘው የቦታ ስፋት 230 ካ.ሜ. የሆነ 50 ቅጠል ቆርቆሮ የፈጀ አራት ክፍል የመኖሪያ ቤትና ቦታ ግምቱ መነሻ ዋጋ ብር 312,001.87/ሶስት መቶ አስራ ሁለት ሺህ አንድ ብር ከሰማኒያ ሰባት ሳንቲም) ከመነሻ ዋጋው በታች ቢሆንም ከቀረቡት ተጫራቾች መካከል ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ስለሚሸጥ ሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ንብረትነቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ ከ3፡00-6፡00 ሰዓት ጨረታውይካሄዳል፡፡ ይህንን ቤትና ቦታ መግዛት የሚፈልግ በቦታው ተገኝቶ ተጫርቶ መግዛት ይችላል። የጨረታው አሸናፊ አካል የሆነ ያሸነፈበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ ማስያዝ ያለብዎት መሆኑን አውቀው መጫረትና መግዛት የሚፈልጉ በቦታው ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰሜን ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ፍ/ቤት
