የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በከምባታ ዞን በዶዮ ገና ከተማ አስተዳደር በልዩ ስሙ ገበራ ሰፈር የሚገኘውን 520 ካሬ ላይ ያረፈውን መኖሪያ ቤት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የቤት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በከምባታ ዞን በዶዮ ገና ከተማ አስተዳደር በልዩ ስሙ ገበራ ሰፈር የሚገኘውን 520 ካሬ ላይ ያረፈውን መኖሪያ ቤት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው መሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ብቻ በሲፒኦ ፣ በካሽ ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ በነጻ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሰነዱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናልና 1 ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥው የስራ ቀን ይከፈታል።
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 771 0586/0511/083
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ወራቤ
