የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት የጽሕፈት መሳሪያ ፣ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ፣ የፅዳት ዕቃዎች ፣ ደንብ ልብስ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈፀም ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2015 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና መስክ ጽ/ቤቶች
- የጽሕፈት መሳሪያ
- የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች
- የፅዳት ዕቃዎች
- ደንብ ልብስ
- ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
- የሥልጠና መስተንግዶ
- የሕትመት ሥራ
- የደንብ ልብስ ሰፌት
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማና ካለማዳሪ ግዥ
- የጭነት አገልግሎት
- ማሸነሪ ጥገና
- የአጥርና የቤት ጥገና
- የተሽከርካሪ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈፀም ይፈልጋል።
- ስለዚህ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ በአገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ) በጥሬ ብር ወይም በሰርቲፋይድ ቼh (CPO) ለማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 17 (አስራ ሰባት) በመውስድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በሁለት ኮፒ በማሸግ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በፅዳት ዕቃዎች ፣ በጽህፈት መሳሪያዎች ፣ በቋሚ አላቂ ዕቃዎች እና በደንብ ልብስ ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ላይ የዕቃውን ናሙና በፎቶ ግራፍ ማቅረብ አለባቸው:
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጐ በ8:15 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም
- ተጫራቾች ባሸነፉት የዕቃ ዋጋ ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ: ምሥራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ መመሪያ ፊት ለፊት ወጋገን ሆቴል አጠገብ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 057 660 3936/057 661 2054/
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት (ነቀምቴ)
