ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ስማርት ፓርኪንግ ቴክኖሎጂ እና አውቶማቲክ ሪትራክቴብል ጌት አቅርቦትና ገጠማ ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር RE-CC/
NCB/G/06/2014/21
ስማርት ፓርኪንግ ቴክኖሎጂ እና አውቶማቲክ ሪትራክቴብል ጌት አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ጨረታ
- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ስማርት ፓርኪንግ ቴከኖሎጂ እና አውቶማቲክ ሪትራክቴብል ጌት አቅርቦትና ገጠማ አገልግሎት ግዥ ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት በመንግሥት ግዥ አዋጅ በተገለጸው ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓት መሠረት ይሆናል: የስማርት ፓርኪንግ ቴክኖሎጂ እና አውቶማቲክ ሪትራክቴብል ጌት አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆነ ተጫራች እና ከአቅርቦቱ ጋር አግባብነት ያላቸው ሆኖ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ታክስ ክሊራንስ፣ ከንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የአቅራቢነት ዝርዝር (Supplier List) ፕሪንት አርጎ ማምጣት አለባቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ITN እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርትፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ከፍለው የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው አድራሻ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 06 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡ ዘግይተው የቀረቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺ ብር/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:፡
- የጨረታው ሰነድ የሚገባበት አድራሻ ጉምሩh ኮሚሽን ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 4ኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ቢሮ፡፡
- ኮሚሽኑ በከፈልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው::
ጥላሁን ገሰሰ አደባባይ መሿለኪያ አካባቢ የሚገኘው /ይርጋ ኃይሌ ፕላዛ ህንጻ/ የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ
ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን 4ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር: 011-676-3815
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን
