መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.በቆሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሰብል ሽያጭ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.ሰብል በቆሎ 5,000(አምስት ሺህ) ኩ/ል ባህር ዳር ከተማ መጋዝን፣ 5,000(አምስት ሺህ)ኩ/ል ዱርቤቴ መጋዝን፣ 5,000.00(አምስት ሺህ)ኩ/ል ሰ/ሜጫ ወረዳ ወተት አባይ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ መጋዝን 2,150.00(ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ) ኩ/ል ደ/አቸፈር ወረዳ ቀልጠፋ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ አሁሪ ቅርጫፍ መጋዝን በድምሩ 17,150.00(አስራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ) ኩ/ል በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ንግድ ፈቃዱ ላይ የተቀመጠው የስራ አስኪያጅ ስም እና ቅጹ የሞላው ሰው ስም አንድ አይነት መሆን አለበት፡፡ ተወካይ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ ማየያዝ አለበት፡፡
- ቅዳሜ እስከ 6:30 ለዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- የሚሽጠው መጠን በ20 በመቶ ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፡፡
- አሽናፊ የሚለየው በተናጥል (በየሎቱ/) ይሆናል፡፡ አሸናፊው የአሸነፋን ሰብል በፍትህ ለውል ምርመራ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል/ይሸፍናል/፡፡
- አሽናፊው የአሽነፈውን ሰብል በእራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ሊያነሳ/ሊወሰድ/ነው፡፡
- በየሎቱ ብቻ ለይቶ መሙላት የሚቻል ሲሆን ሁሉንም ሎት መሙላትም ይችላሉ፤ መጠኑን ግን ቀንሶ መሙላት አይቻልም፡፡
- ሰብሉ የሚገኝበት ቦታ ባህር ዳር ከተማ፣ ዱርቤቴ ከተማና ቢኮሎ ከተማ እና ቀልጠፋ አሁሪ ቅርጫፍ ሲሆን ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት ይችላሉ፡፡
- አሽናፊው የትራንስፖርትና የወዛደር ማሽጫኛ እና የትራንስፖርት ውጪ በአሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ በህ/ስ/ማ/ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 55/2012 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 0918341125/0911590534 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.
