Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Jul 2022, 12:59 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Tour And Travel

በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ለ2015 በጀት ዓመት የተለያዩ የመጫን አቅም ያላቸዉ ተሽከርካሪዎችን ለሰራተኞች ማመላለሻ አገልግሎት የሚውሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።


የተሽከርካሪ አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

 

የጨረታ ቁጥር ግ.ጨ.ቁ መ.ኢ.ኮ 01/2015

በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ለ2015 በጀት ዓመት ከታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የመጫን አቅም ያላቸዉ ተሽከርካሪዎችን ለሰራተኞች ማመላለሻ አገልግሎት የሚውሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም ቀጥሎ የተጠቀሱትን መመሪያዎች የምታሟሉ ተጨራቾች በጨረታው እንድትሰተፉ ተጋብዛችኃል፡፡

ተ.ቁ

የተሽከርካሪ አይነት

ብዛት

ደረጃ

የመጫን አቅም

የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ

1

ኮስትር ባስ

03

1ኛ ደረጃ (የተሟላ ቴክኒክ)

21-22

20,000.00(ለአንዱ)

2

አውቶብስ

01

1ኛ ደረጃ (የተሟላ ቴክኒክ)

60

23,000.00

3

ሚኒ ባስ ህይሩፍ

01

1ኛ ደረጃ (የተሟላ ቴክኒክ)

15

15,000.00

4

ሚኒ ባስ ህይሩፍ

02

1ኛ ደረጃ (የተሟላ ቴክኒክ)

15

15,000.00(ለአንዱ)

 

 

  1. ተጨራቾች የሚያቀርቧቸዉ መኪኖች 1ኛ ደረጃ (የተሟላ ቴክኒክ) ሆነዉ የተሠጣቸዉን ማስረጃዉን ኮፒዉን አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  2. የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ ቁጥር ግ.ጨ.ቁ መኢኮ 01/2015 በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) ፋይናንስ ቡድን በመክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  3. 3ኮሌጁ ባቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የአንድ ቀን የኪራይ ዋጋ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላትና ህጋዊ ማህተም፣ፊርማ፣ስልክ ቁጥር እንዲሁም የታደሰ፣ ንግድ ፈቃድ፣ የባለቤትነት መረጋገጫ (ሊብሬ) ፣ተወካይ ከሆኑ የዉክልና ማስረጃ፣የማህበር አባል ለሆኑ ተጫረቾች አባልነታቸዉ የሚረጋገጥበት ከማህበሩ የተሰጣቸዉን ማስረጃዎች፣የኢንሹራንስ እና የንግድ ማስረጃዎችን በሙሉ ኮፒ በማድረግ በፖስታ አሽጎ (ዋናዉንና አንድ ኮፒ) ግዥ ቡድን ባዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።
  4. አሸናፊዉ ተጫራቾች አሸናፊነታቸውን እንደተገለፀ እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ዉል አስሮ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  5. ጨረታዉ ሃምሌ 06/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:31 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡45 ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ እና ታዛቢዎች በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  6. ኮሌጁ ለአፈፃፀም የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  7. ለተጨማሪ ማብራሪየ በመከላከያ ዩኒቨርስቲ የኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ቢሾፍቱ በቀጥታ ስ.ቁጥር 011 433 5163 ወይም 011 433 8400 የዉስጥ መስመር 166/164 ጠይቀዉ መረዳት ይችላሉ።

በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ኮሌጅ

Save Tender