የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የሲኖ መኪና መለዋወጫ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፀውን እቃዎች በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
ምርመራ |
|
1 |
የሲኖ መኪና መለዋወጫ |
ለዋና ቢሮ |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ::
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የተ.እ.ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ቁጥር እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል/ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም ለ60 ቀናት የጸና ያለቅድመ ሁኔታ እንደ ተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ በአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ስም በማሰራት ብር 50,000(አምሳ ሽህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን የእቃ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 50 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን ዋጋ እና የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ከአንድ ዋና /ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ኮፒ/ ቅጅ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት ዋናው መ/ቤት አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 26 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ20ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:30 ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-35-76 መደወል ይችላሉ፡፡
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት
