Tender Detail

Tender Details


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የጽህፈት መሳሪያ፣ የፕሪንተር ቀለም፣ የጽዳት እቃና የመኪና መለዋወጫ ግዥ

Amhara National Regional State Bureau of Agriculture (አማራ ክልል ግብርና ቢሮ)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር/No ግቢ/ግፋ/2803 /19

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ሎት 01 የጽኅፈት መሳሪያ, ሎት 2 የፎቶኮፒና የፕሪንተር ቀለም ሎት 3 የጽዳት እቃ ሎት 4 ለመኪና መለዋወጫ እቃ ፣ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል:: ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

  1. በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ መታደሱን የሚገልፅ ንግድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ::
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት,
  3. የግዥው መጠን ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  5. የሚገዙት እቃዎች ሎት 01 የጽኅፈት መሳሪያ ሎት 2 የፎቶኮፒና የፕሪንተር ቀለም ሎት 3 የጽዳት እቃ ሎት 4 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃወች ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ የቀበው ሰነድ ማህተም በማድረግ እንዲመለስ::
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ ብር በቁርጥ ሲሆን ሎት 01 የጽኅፈት መሳሪያ ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺ ብር/ ሎት 2 የፎቶኮፒና የፕሪንተር ቀለም 20,000.00 /ሀያ ሺ ብር/ ሎት3 ጽዳት እቃ 40,000.00 /አርባ ሺ ብር/ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ ብር 60,000.00 /ሁለት መቶ ሀምሳ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው:: ማንኛውም ተጫራች የጨረታ/የመወዳደሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነዱን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን እና የፋይናንሸያል ሰነዱን ከአንድ ላይ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 017 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ጨረታው ክፍት ሁኖ በአየር ላይ ይቆያል::
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 11ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4:00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል::
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  10. በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር27ድረስበመገኘትወይምበስልክቁጥር0582266431/0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
  11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም::
  12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ::

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ

Summary
Amhara Regional State Bureau of Agriculture invites bids in four lots: stationery, photocopy and printer toner, cleaning materials, and vehicle spare parts.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender