የሰሜን ሸዋ ዞን አብቹና ኘአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመንገድ ጠጠር ማልበስና ጥገና የማሽን ኪራይ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ፕአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ማዕከላዊ ዞን የአብቹና ኘአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለአብቹና ኘአ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ለተለያዩ ቀበሌዎች መንገድ፤ መንዲዳ ዙሪያ ማግል (2 ኪ.ሜ ) ሁለተኛ ዙር ጠጠር ማልበስ እና ዳዮሌ አብደላ ሉጎ (4 ኪ.ሜ) የመንገድ ጥገና የሥራ ግንባታ የሚያስፈልጉትን ማሽኖች ተከራይቶ ለማሰራት ይፈልጋል::
በዚሁ መሠረት፤
- ተጫራቾች በዘርፉ የማሽን ኪራይ ፈቃድ ያለውና 2019 የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑን ግብር የከፈለ በጨረታው መወዳደር ይችላል::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ለመከፈሉ ከገቢዎች ደብዳቤ ማቅረብ አለበት::
- የአቅርቦት ዝርዝር (supply list) መረጃ ማቅረብ አለበት::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ (CPO) 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለአብቹና ኘአ ገንዘብ ጽ/ቤት የተጻፈውን ኦርጂናል የቴክኒክ ሰነድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የውል ማስከበሪያ (performance bond) 10% ከጠቅላላ ዋጋ ማስያዝ አለበት:: አሸናፊ ተጫራች የጨረታ ውል ማስከበሪያ (CPO)ያላቀረበ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ለመንግስት ገቢ ሆኖ ሌላ ተጫራች እንዲያቀርብ ይደረጋል::
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ማሽኖች ሁሉ አንድ ላይ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት:: ከፋፍሎ መወዳደር አይቻልም::
- ፖስታው የሚቀርበው በተወዳዳሪ መመሪያ ላይ በተጻፈው ሁኔታ ተፅፎ መቅረብ አለበት::
- የተወዳዳሪ ስም የፕሮጀክት ባለቤት ስም፣ የፕሮጀክት ስም፣ የተወዳዳሪ ፊርማና ማህተም፣ የተወዳዳሪ አድራሻና የፕሮጀክት ባለቤት በፖስታ ላይ በግልፅ መፃፍ አለበት::
- ለውድድር በቀረቡት ሰነዶች ሁሉ ላይ የድረጅቱ ሊቀመንበር ስምና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም በግልጽ መገኘት አለበት::
- በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም::
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ሃሳብ መቀየር ወይም ማሻሻልና ከጨረታ ውስጥ እራሱን ማውጣት (ማግለል) አይችልም:: እንደዚሁም ማንኛውም ተወዳዳሪ ከተባለው ሰዓት ወጪ ሰነድ መግዛት ሆነ መመለስ አይችልም::
- ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ለማጭበርበርም ሆነ ለማሳሳት ሙከራ ያደረገ ከጨረታ ይሰረዛል::
- ተወዳዳሪዎች በመንግስት ግዥ ቅጣት የሌላቸውና ያልተወገዱ መሆን አለባቸው::
- አሸናፊ ተጫራች ማሽኖችን ነዳጅና ትራንስፖርት እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን እራሱ መሸፈን አለበት::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአብቹና ኘአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 700 (ሰባት መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ22ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የፕሮጀክት ኮሚቴዎችና የቴክኒክ ኮሚቴዎች በተገኙበት በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 4:30 በአብቹና ኘአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የሚከፈት ሆኖ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::
- ተወዳዳሪው ሁለት ጨረታን አንዴ ካሸነፈ በራሱ ምርጫ አንዱን ይወስድና በቀጣይ ላለው ግን ሙሉ በሙሉ በመጀመሪያ ያሸነፈ ተወዳዳሪ ወስዶ የሚሰራ ይሆናል::
ማሳሰቢያ:- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የቦታ ርቀት እየጨመረ ሲሄድ የባጀ ዋጋ እየጨመረ ካልሄደ ድርጅቱ ከውድድር ውጪ ይሆናል::
አድራሻ:- አብቹና ኘአ ወረዳ መንዲዳ ከተማ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-21-51-77-27 ይደውሉ::
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ማዕከላዊ ዞን የአብቹና ኘአ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Summary
Abichuna Gne'a Woreda Finance Office (North Shewa, Oromia) invites bids to rent machinery for road gravelling and maintenance on two rural roads (2 km and 4 km) for the woreda roads and transport office.
