የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወንበሮችና የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማ/ት/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታውቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2019 በጀት በ2ኛ ሩብ ዓመት የተለያዩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወንበሮችን እና የፈርኒቸር እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራች ማሟላት የሚገባቸው
- ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
- የዘመኑ ግብር የከፈለ /ከኢትዮ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን/ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- ተወካይ ከሆነ /ከሆነች/ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ቫት ሳይጨምር በመሙላት በዘርፉ ድምር ከተሰራ በኋላ የቫት ድምር ለብቻ መቀመጥ አለበት።
- ተጫራች የአንድ ዋጋ ከሞላ በኋላ ወደ ጎን አባዝቶ እና ወደ ታች ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል።
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሚቀርቡት የእቃ ዝርዝሮች መሰረት በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል። ሁሉም እቃዎች ዋጋ መሞላት ይኖርባቸዋል።
- በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ስርዝ ድልዝ ካለ እና ፍሉድ ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል። ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ ኮፒውን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ እንዲሁም በየዘርፉ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽጎ የሚወዳደርበትን ዘርፍ በመፃፍ ማቅረብ አለበት። በዚህ መሰረት ሶስቱንም ፖስታዎች ለየብቻ ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልክ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ C.P.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
- የጨረታ አሸናፊዎች ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ C.P.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን ከማሰልጠኛ ት/ቤቱ ፋይናንስ ዴስክ በስራ ቀንና ሰዓት ከ17/03/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 27/03/2017 ዓ/ም ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን 28/03/2019 ዓ/ም ከጥዋቱ 02:00 እስከ 07:00 ሰዓት ድረስ በማ/ት/ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት አለባቸው። በዚሁ ቀን 28/03/2017 ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በማ/ት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 07:30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ማ/ት/ቤቱ በሚሰጠው የዕቃ አቅርቦት ትዕዛዝ መሰረት በራሱ ትራንስፖርት ወጭ ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በማ/ት/ቤቱ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱን አረጋግጦ ማስረከብ አለበት። የጥራት ኮሚቴው ካልተቀበለው ቀይሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት። መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሚገጣጠሙ ወንበሮችን ሙያተኛ በማምጣት አስተካክሎ በመግጠም የማስረከብ ግዴታ አለበት።
- አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሪጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።
- ማ/ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታውን አሸናፊ ከሆነ ድርጅት ማ/ት/ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ በዘርፉ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
በዚህ ማስታወቂያው ያልተገለፁ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መምሪያ መሰረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል። ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0587600018 በስራ ሰዓት ደውሎ ማረጋገጥ ይችላሉ።
የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት
Summary
Birsheleko Basic Military Training School (Ministry of National Defense) invites open bids to supply assembly hall chairs and various furniture items, with installation of the hall chairs.
