የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎችና የፕሪንተር ቀለሞች ግዥ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል እስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ:-
ሎት 01. የጽህፈት መሳሪያ
ሎት 02. የጽዳት ዕቃዎች
ሎት 03. የፕሪንተር ቀለሞችና ተዛማጅ ዕቃዎችን አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል ::
- ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፤ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ ቫት ተመዝጋቢነት እና ቲን ተመዝጋቢነት ሠርተፍኬት፤ እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሲገዙ ሲመጡ ኦርጂናሉንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው::
በመሆኑም ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 100453748693 በማስገባት የባንክ እስሊፑን በመያዝ ዘወትር በስራ ሠዓት ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ::
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ቼክ ፤ በሁኔታዎች ላይ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና
- ለሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
- ለሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ)
- ለሎት 3 የፕሪንተር ቀለሞችና ተዛማጅ ዕቃዎች 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ)
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በየሎት በማከፋፈል እና የሎት ቁጥሩን ሰነዱ ላይ በመጻፍ በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ :: የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንስግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ይከፈታል :: የጨረታ መዝጊያና መከፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል :: በመክፈቻው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም :: ተጫራቾች ሰነድ ሲያስገቡ ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በአንድ ፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው ::
- አሸናፊው ድርጅት በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንስግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት ::
- ተወዳዳሪዎች ጨረታ ለማስገባት ሲመጡ ከሎት 1-3 ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ድርጅት ዋጋው አይታይለትም::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047331-2694/0473312790 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ
አድራሻ ቦንጋ ከተማ
