Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsehay Insurance S.C (TISC) (ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 25111111970
  • Websitehttps://tsehayinsurance.com/
  • Deadline01 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 100,000.00 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:30 ሰዓት፣ 4ተኛ ፎቅ በኩባንያው አዳራሽ
  • Sector Water and Water Works , Water Well Drilling and Water System Installation , Water Construction

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ለሕንጻ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የከርሰ ምድር ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና ልማት

Tsehay Insurance S.C (TISC) (ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

በድጋሚ የወጣ የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- የጨረታ መለያ ቁጥር TSI/PPA/GPW/010/2026

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ በአራዳ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 05 (ፒያሳ ደጃች ውቤ አካባቢ) ላስገነባው 1/2B+2B+2B+G+9 ድብልቅ አገልግሎት ሕንጻ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውል የከርሰ ምድር ውሃ ማምረቻ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ ግንባታ፣ ልማት (ዲቨሎፕመንት)፣ የውሃ መሳብ (ፓምፒንግ) ሙከራዎች እና የውሃ ጥራት ምርመራ ስራ ብቁ የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

1. የተጫራቾች ብቃት እና ተፈላጊ ሰነዶች

-ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሰነዶች እና ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል:-

  • በዘርፉ (የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ / የውሃ ስራ ተቋራጭነት) የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ማስረጃ፣ የዘመኑን ግብር በአግባቡ ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ የታክስ ክሊራንስ ፤
  • በከርሰ ምድር ውሃ ማምረቻ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ልማት ስራ በቂ ልምድ ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ የስራ ልምድ ማስረጃ (የመልካም ስራ አፈጻጸም ወይም የውል ቅጂ)፣
  • በቂ የቁፋሮ ማሽነሪዎች (Rig)፣ መሳሪያዎች እና ብቁ የቴክኒክ ባለሙያዎች እንዳሏቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣

2. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድ እና አከፋፈል

  • ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የስራ መግለጫ እና ሰነድ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:00 እስከ ከሰዓት 11:00 በፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::

3. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security)

  • ተጫራቾች ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ስም ተሰርቶ ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::

4. የጨረታ ማስረከቢያ እና መክፈቻ ጊዜ

  • የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ 4:00 ሰዓት::
  • የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:30 ሰዓት 4ተኛ ፎቅ በኩባንያው አዳራሽ ይከፈታል።
  • ከተጠቀሰው ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም::

5. ተጨማሪ መረጃ

  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር Tel-011-111-97 70/71 or 011-111-98 27 ይደውሉ::

የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

Summary
Tsehay Insurance S.C. re-advertises a tender for drilling, constructing, developing and pump-testing a groundwater well to supply drinking water to its mixed-use building in Arada (Piassa), Addis Ababa.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender