የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ፣ የትምህርት ቁሳቁስ፣ የጄኔሬተር ግዥና የመጽሐፍ ህትመት
South Ethiopia Region Education Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02 ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትም/ቢሮ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት በተለያዩ በጀት በመጠቀም የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተፋጠነ ትምህርት የትምህርት ቁሳቁስ፣ የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት የድጋፍ መስጫ መሳሪያዎች እና የሞኒቶሶሪ ኪቶች፣ ሞጁል ህትመት፣ የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል መማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍ ህትመት እና የጄኔሬተር ግዥ
በዩኒሴፍ በጀት
- ኤሌክትሮኒክስ
- የትምህርት ቁሳቁስ
- የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት የድጋፍ መስጫ መሳሪያዎች
- የሞኒቶሶሪ ኪቶች
- የልብስ መስፊያ ማሽን ከነቁሳቁሶቹ
- ሞጁል ህትመት
በመደበኛ በጀት
- Generator
- የ7ኛ ክፍል ሎት 1 እና የ8ኛ ክፍል ሎት 2 መማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍ ህትመት ግዥ ለመፈጸም በሥራ መስክ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶችን ለማወዳደር ይፈልጋል::
በዚሁ መሠረት ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሴርተፊከት፣ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበት መረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል::
- ተጫራቾች ትምህርት ቢሮ ቁጥር 18 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በየሎቱ እና በየጨረታ ሰነዱ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- የፋይናንሻል ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ አሽጎ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮ ቁጥር 18 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፀው መሠረት ጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2:30-6:30 ሰዓት ሰነዱ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ገብቶ ወድያውኑ ታሽጎ ከሰዓት 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0467752359 መጠየቅ ይችላሉ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ /ጂንካ/
Summary
South Ethiopia Region Education Bureau (Jinka) invites bids for electronics, education materials, special needs and Montessori kits, sewing machines, module and textbook printing, and a generator.
