Tender Detail

Tender Details

  • Company በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline05 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 300 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 9,000 እና ከዚያ በላይ (የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ)
  • opening date4:30 ሰዓት
  • Sector Medical Equipment and Supplies , Veterinary Equipment and Supplies

የሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የእንስሳት መድሃኒቶች ግዥ

በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኤግገ/09/ 250 /2019

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለኤ/ግ/ወረዳ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ለእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚያስፈልጉ የተለያዩ መድሃኒቶችን በግልፅ የጨረታ አግባብ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ:-

1.ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገበ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የግዥ መጠኑ ብር 500,000 እና ከዚህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት መረጃ ማቅረብ የሚችል፣

2ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 9,000/ዘጠኝ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ማሲያዝ እንደሚጠበቅባቸው ይኸውም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፅ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል::

3.ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ወቅት እንዲገኙ አይገደዱም ነገር ግን በጨረታው መገኘት አለብን ብለው ካሰቡ መገኘት ያለበት አካል የተጫረተው ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው አካል ኦርጅናል የውክልና ማስረጃውን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል::

4.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 6 የማይመለስ 300 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፣

5.ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ16/3/2019 ዓ.ም እስከ 25/3/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ማለትም በ26/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ 4:30 ሰዓት ይከፈታል::

6.ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም ::

7.ተጫራቾች ለወሰዱት የተጫራች መመሪያ /የጨረታ ሠነድ/ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ሙሉ በሙሉ መመለስ ይጠበቅባቸዋል::

8.በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው አሸናፊ ስለሚሆን ሙሉ በሙሉ ጨረታው ላይ ዋጋ መሞላት አለበት ይህ ካልሆነ ግን ከውድድር ውጪ ያደርጋል፣

9.አሸናፊ የሆነው ተጫራች የእንስሳት መድሃኒቶቹን በኤ/ግ/ወረዳ እንስሳትና አሳ ሀብት ጽ/ቤት ንብረት ክፍል በሞዴል 19 ገቢ ማድረግ አለበት:: ገቢ ያደረገበትን የእንስሳት መድሃኒት ሞዴል 19 በመያዝ ክፍያ ይፈፀምለታል::

10.ጽ/ቤቱ ግዥውን በ20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል::

11.ተጫራቾች ዋጋቸውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም የሚኖር ከሆነ ከጨረታ ውጪ ያደርጋቸዋል፣

12.ተጫራቾች በሞሉት አጠቃላይ ድምር ላይ አርቲሜቲክ ቼክ ሲሰራ 3% ከአስቀመጡት ዋጋ ላይ የድምር ስህተት ከፍና ዝቅ ካለ ከጨረታ ውጪ ያደርጋቸዋል፣

13.ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

14.ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ ጠቅላላ ድምር ደምረው ማስቀመጥ አለባቸው::

ማሳሰቢያ:- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል::

በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት

Summary
Efratana Gidim Woreda Finance Office (North Shewa, Amhara) invites bids to supply assorted veterinary drugs for the woreda livestock and fishery office.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender