የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ አንድ ባለ 196-257 HP ሎንግ ሪች ሃይድሮሊክ ኤክስካቫተር ለመግዛት በድጋሚ ያወጣው ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ (ቁጥር እግጨ/0019ኦኩስፋ-2/2019)።
Ethiopian Sugar Industry Group Omo Kuraz No-2 Sugar Factory
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- እግጨ/0019ኦኩስፋ-2/2019 ዓ.ም
- በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦም ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጥቅል 1 Purchase of One units of 196 - 257 HP Long Reach Hydraulic excavator ለመግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ120 ቀን የባንክ ዋስትና /BID BOND/፣ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር/supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውሎ በአስራ ስድስተኛው ቀን ይከፈታል። የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7:00-10:30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት፣ ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተጠቀሰው ነው።
5.1. ኦም ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኡ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ፡፡ ስልክ ቁጥር: 09-91-14-94-85/0986862766/ 0940209464 አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ - ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች አንድ ላይ የጨረታ የማስከበሪያ ዋስትና ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የማሽኑ ርክክብ የሚፈፀመው ኦም ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር የሚገኝበት ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሰላማጎ ወረዳ ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው።
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦም ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ Tel- 0940209464 ኃይል ውሃ
አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ Tel: 09-91-14-94-85 /0986862766 አዲስ አበባ
የኦም ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
Summary
Omo Kuraz No. 2 Sugar Factory (Ethiopian Sugar Industry Group) re-tenders the purchase of one 196-257 HP long-reach hydraulic excavator, delivered to the factory in South Omo zone. Bidders need a licence, TIN, VAT, supplier listing and tax clearance.
