Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ሳሪስ አቦ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ጎን 200 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114709095
  • Websitehttps://ethioagri.com/
  • Deadline10 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price3000(ሶስት ሺህ ብር)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 2% CPO ወይም የባንክ ዋስትና
  • opening dateታህሳስ 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Sector Chemicals And Reagents , Pesticides, Insecticides And Herbicides

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ) የአረም፣ የተባይና የፈንገስ ማጥፊያ የግብርና ኬሚካሎች ግዥ በ3 ሎት ያወጣው የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር SSS-AC-03-2026)።

Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡ SSS-AC-03-2026

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ) (Ethiopian Agricultural Businesses Corporation Agricultural Input Supply Sector) ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የግብርና ኬሚካሎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ (NCB) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሚገዙ የግብርና ኬሚካሎች ዝርዝር (Lots):
ምድብ 1 (Lot 1)፡ የአረም ማጥፊያ ኬሚካሎች (Herbicides)
ምድብ 2 (Lot 2)፡ የተባይ ማጥፊያ ኬሚካሎች (nsecticides)
ምድብ 3 (Lot 3)፡ የፈንገስ/በሽታ ማጥፊያ ኬሚካሎች (Fungicides)

በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት እና በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 3000.00 ( ሶስት ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ እስከ ታኅሣሥ 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ዕለት ታህሳስ 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ ዋና አዳራሽ ይከፈታል።

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቃሊቲ የባቡር መጨረሻ በአዋሽ ባንክ መግቢያ ወረድ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ባለው ሕንፃ ምድር ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ።
Email: aweln@Ethioagri.com

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Summary
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (Agricultural Input Supply Sector) buys agrochemicals in 3 lots: herbicides, insecticides and fungicides, by national competitive bidding. Licensed, VAT-registered suppliers on the procurement agency list may bid.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender