የዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቢሮና ሾፕ ጥገና ግንባታ ስራ
Dalocha Poly Technic College (ዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
የጨረታ መስታወቂያ
በማዕ/ኢ./ክ/መ/ በስልጤ ዞን በዳሎቻ ከተማ አስተዳደር የዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የቢሮ እና ሾፕ ጥገና ግንባታ ስራ በዘርፉ የተደራጁ ማህበራትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል። ስለሆነም ደረጃቸው G.C/B.C-9 እና ከዛ በላይ ፤
- የዘመኑ ግብር አጠናቀው የከፈሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፤
- የታደሰ የንግድ ፍቃድና የስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- የጨረታ ዋስትና 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፤
- የኦዲት ሪፖርት እና የማህበሩን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ስራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ
- የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገለጽ የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
ማህበራት ሰነዱን ከዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር -----በማቅረብ የማይመለስ ብር 300 ( ሶስት መቶ ብር ብቻ ) (መክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤ የጨረታ ሰነዱ ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ ፤ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸጋ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ ተከታታይ) ቀናት ውስጥ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሰጥኑ በ21ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8:30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ:-
ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል።
- የተወዳደሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መከፈቻ ቀኑን አይለውጥም።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆና በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የተሞላው ዋጋ መገለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያላጠናቀቁት ሁለት እና ከዛ በላይ ፕሮጀክቶች ይዘወው አፈጻጸማቸው 70 % መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ካልቀረበ ከጨረታው ይሰራዘሉ።
ለበለጠ መረጃ:- ስልክ ቁጥር 0925746727ደውሎ ወይም ዳ/ፖ/ቴ/ኮ/ ግዥ ክፍል ብሮ ቁጥር ቀርቦ መጠየቅ ይችላል።
