Tender Detail

Tender Details

  • Company የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 222 14 79
  • Website
  • Deadline12 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 1,000 (የማይመለስ)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ሎት ብር 250,000.00 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበ20 ኛው ቀን በ8:30 ሰዓት (ቴክኒካል)
  • Sector Construction , Water and Water Works , Water Construction

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ዋናው መ/ቤት) የዙ-ሃሙሲት መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት በንዑስ ተቋራጭ የአገልግሎት ግዥዉን ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 08/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

አገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየጨረታ ቁጥር NCB WWC 08/2019

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ዋናው መ/ቤት) የዙ-ሃሙሲት መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት በንዑስ ተቋራጭ የአገልግሎት ግዥዉን ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 08/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ:

ተ. ቁ የሎት ቁጥር ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር/ዓይነት Summery of goods መለኪያ ብዛት ምርመራ
1 ሎት-1 Four Faucet Water Point (Twenty in Number በቁጥር 1  
2 ሎት-2 Six Faucet Water Point (Seven in Number) በቁጥር በቁጥር 1  

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል::

  1. የዘመኑን ግብር ከፍለዉ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/፤የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ መሆን አለበት:: ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸዉን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባዉ ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል::
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ60 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለሎት-1 ብር 250,000.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ ብር/፤ለሎት-2 250,000.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ ብር/በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸዉ::
  3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 /ሃያ/ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሽህ ብር/ በውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ከኮርፖሬሽኑ ዋና ግቢ ከጠቅላላ ሒሳብ ክፍል ቢሮ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ቦንጋ ሆቴል ገባ ብሎ 100 ሜትር በመሄድ መግዛት ይችላሉ::
  4. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸዉን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸዉን በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል/ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  5. የቴክኒካል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግቢ ግዥና አቅርቦት ዳይሬክትሬት ቢሮ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል::
  6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር- 058222-14- 79 መጠየቅ ይቻላሉ::
  8. ማሳሰቢያ:- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መግዛት ብቻ እንጅ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት የሚቻለው ባህርዳር ዋናው መስሪያ ቤት መሆኑን እንገልፃለን ::

አድራሻ: - ውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት
ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 የድሮው አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ፖ.ሣ.ቁ 106
ስልክ ቁጥር 0582221479
ፋክስ/ባህር ዳር

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Summary
Water Works Corporation invites subcontractors to build four-faucet and six-faucet water points for the Zu-Hamusit drinking water project in two lots. Bids are submitted at its Bahir Dar head office.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender