የሲዳማ ቡና አብቃይ ገበሬዎች ኀ/ሥራ ዩኒየን የውጭ ኦዲት አገልግሎት
የሲዳማ ቡና አብቃይ ገበሬዎች ኀ/ሥራ ዩኒየን
የሂሣብ ምርመራ ጨረታ
ድርጅታችን የሲዳማ ቡና አብቃይ ገበሬዎች ኀ/ሥራ ዩኒየን በቡና ኤክስፖርት ሥራ ላይ የተሠማራ ሲሆን እ.ኤ.አ ነሐሴ 31, 2026 የተጠናቀቀውንና በ "IFRS" የተሠራ የአንድ ዓመት ሂሣብ በውጭ ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾች የጨረታውን ፕሮፖዛል ይህ ማስታወቂያከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ።
- በኢትዮጵያ የሂሣብ አያያዝና ኦዲቲንግ ቦርድ ወይም እሱ በሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለው የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል’
- በሀገሪቱ ህግ መሠረት ኦዲት ሥራ ለመስራት የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን የተመዘገበና ማስረጃ ማያያዝ የሚችል፣
- ተወካይ ሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ ምርመራ ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት ኅብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ የመረመረ፣
- የኅብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎች በሥራ ላይ ማሰማራት የሚችል’ ይህ ሳይሆን ለሚከሰተው ማንኛውም ኪሳራና ችግር አስቀድሞ ኃላፊነቱን የሚወስድ’
- የተዘጋጀ TOR ከድርጅታችን መውሰድ የሚችል።
ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
አድራሻ: አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 በዩኒየኑ ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ
ስልክ: 011 440 7165 እና 0911 40 9994
የሲዳማ ቡና አብቃይ ገበሬዎች ኀ/ሥራ ዩኒየን
Summary
Sidama Coffee Farmers Cooperative Union invites licensed external auditors to audit its one-year IFRS financial statements. Auditors must be registered with the Ethiopian Commodity Exchange Authority.
Not stated in the notice: opening date, bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
