Tender Detail

Tender Details


የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን የቀላል ተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ፣ የሕንፃ መሳሪያ እቃዎች እና የሰራተኛ ደንብ ልብስና ጫማ ግዥ በ3 ሎት ያወጣው የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር መ.ሠ.ፋ/ብ.ግ.ጨ-06/2019)።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር መ.ሠ.ፋ/ብ.ግ ጨ-06/2019

በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በስሩ ለሚገኙት ክፍሎች ለጠ/አገልግሎት ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ እና ባትሪ
ሎት 2 የተለያዩ የሕንፃ መሳሪያ እቃዎች
ሎት 3 የተለያዩ የሰራተኛ የደንብ ልብስ እና ጫማ

በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ/VAT Registration Certificate/፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡ እና የቲን ሰርቲፊኬት የብቃት ሰርቲፊኬት tax clearance certificate የመንግስት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ሰርቲፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር በየሎቱ 500/ አምስት መቶ / ብር በመክፈል መ.ሰ.ፋ.ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 015 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም ሎት 1 ብር 20,000 / ሃያ ሺህ ብር ሎት 2 ብር 20,000 / ሃያ ሺህ ብር ሎት 2 ብር 20,000 / ሃያ ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረለት /ሲ.ፒ.ኦ/ በሁኔታላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ብቻ በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ስም ከጨረታው ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናል እና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 015 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ እንዲሁም ተያያዥ ዶክመንቶች ማቅረብ አለባቸው።
  5. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ 8:00 ሰአት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:30 መሰፋ ግዥ ክፍል ይከፈታል።
  6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
  7. በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  8. ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው ላንድ ማርክ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0115572752

መከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን

Summary
Ethiopian Defense Forces Foundation buys light vehicle tyres and batteries (Lot 1), building materials (Lot 2) and staff uniforms and shoes (Lot 3). Licensed, VAT-registered suppliers listed with the procurement agency may bid.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender