በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም 1. የደንብ ልብስ 2. አላቂ የፅዳት እቃዎች 3. አላቂ የፅህፈት መሳሪያ 4. የኤሌክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር እቃዎች 5. የህዝብ ትራንስፖርት 6. የመስተንግዶ 7. የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር 002/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም 1. የደንብ ልብስ 2. አላቂ የፅዳት እቃዎች 3. አላቂ የፅህፈት መሳሪያ 4. የኤሌክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር እቃዎች 5. የህዝብ ትራንስፖርት 6. የመስተንግዶ 7. የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል። ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ፍቃድ ያላቸው እና ሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የቅራቢነትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በፖስታ ማቅረብ የሚችሉ። ለሎቶች የተቀመጠው በኢትዮጵያ ብር
- ሎት 1 ደንብ ልብስ 20000
- ሎት 2 አላቂ የፅዳት እቃዎች 12000
- ሎት 3 አላቂ የፅህፈት መሳሪያ 13000
- ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎች 20000
- ሎት 5 የህዝብ ትራንስፖርት 2000
- ሎት 6 መስተንግዶ 2000
- ሎት 7 . የህትመት ውጤቶች 1200
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ በተቋሙ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው እስከ 10ኛው ቀን 11:30 ተዘግቶ በማግስቱ በ11 ኛው ቀን 4:00 ታሽጎ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን የውል ማስከበሪያ ዋጋ 10 % ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፤ ናሙና ማቅረብ የማይችሉትን ቋሚ እቃዎች መ/ቤቱ ባቀረበው ናሙና መሰረት በአካል ማሳየት [...] ነው።
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ እና ውል በተሰጣቸው 5 ቀን ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት ለጽ/ቤቱ ማስረከብ አለበት።
- መ/ቤቱ ጨረታ ሰነድ ላይ ካቀረበው እቃ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
አድራሻ:- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ገርጂ ናይጀሪያ ኢንባሲ አፓርትመንት አጠገብ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ወይም ገርጂ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0116395582
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Summary
Bole Sub-City Woreda 14 Finance Office (Addis Ababa) seeks suppliers in 7 lots: uniforms, cleaning items, stationery, electronics and furniture, public transport, catering and printing. Open bid.
