Tender Detail

Tender Details

  • Company በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118-34-09-79
  • Website
  • Deadline07 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 5,000 CPO
  • opening dateበዛው ቀን 4:30 ሰዓት
  • Sector Office Supplies and Services , Stationery

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 04/19)።

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04/ 19

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ከዚህ በታች የተጠቀሱ የእቃ ግዥ ለ2019 በጀት ዓመት አወዳድሮ ግዥዎች መፈጸም ይፈልጋል።

ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታዉ እንዲሳተፉ ይጋብዛሉ። በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. አግባብነት ያለዉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመገኘት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱበት የጨረታ ሎት የጽህፈት መሳሪያ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች 5,000 (አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከ ቴክኒካል ሰነድ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀዉ ሣጥን ማስገባት አለባቸዉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ የስራውን ዝርዝር የሚገልጽ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየ ብቻ ዋናውን (ኦርጅናል) እና የማይከፈት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጥቀስ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትን ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 4:30 ላይ ይከፈታል የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በማግስቱ ባለው የስራ ቀን 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡበት የነጠላ ዋጋ በሰነዱ ላይ በመግለጽ ሙሉ አድራሻና ማህተም መጠቀም አለባቸዉ።
  6. የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ማሳሰቢያ፡-

  1. ሙሉ ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ዋጋ ተሞልቶበት ህጋዊ ማህተም እና በየገፁ ፊርማ ተደርጎበት መመለስ አለበት ካልተመለሰ ከጨረታ የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
  2. ለእያንዳንዱ እቃ ሳምፕል መቅረብ አለበት

አድራሻ፡- ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02
ስልክ ቁጥር 0118-34-09-79

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Summary
Kolfe Keranio Sub-City Chief Executive Pool Administration and Finance Office (Addis Ababa) buys stationery and consumable office supplies. Licensed VAT-registered suppliers may bid; samples are required for each item.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender