የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የጥልቅ የመስኖ የዉሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ (ሎት 1) እና የህንፃ መሳሪያዎች ግዥ (ሎት 2) ያወጣው የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 01/2019)።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 01/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት የሚዉል ሎት 01 ጥልቅ የመስኖ የዉሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ ሎት 02 የህንፃ መሳሪያዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና ማግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርቲፍኬት ያላቸው።
- የግዥ መጠኑ ከብር 500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለሎት 1 ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ለየብቻ ኦርጅናልና ኮፒ አሽገዉ ማቅረብ ይጠበቅባቸኋል፤ ለሎት 02 ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ ።
- ተጫራቾች ለሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ 160,000.00/አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ብር/ በCPO ማስያዝ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ለሎት 02 የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይጠበቅባችኋል።
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- ተጫራቾች ለሎት 01 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር /ለሎት 02 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመምጣት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ለሎት 01 ከ 13/03/2019 እስከ 07/04 /2019 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት 11:30 ድረስ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ለሎት 02 ከ 13 /03/2019 እስከ 22/03/2019 ድረስ የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት የሎት 01 በቀን 08/04/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ የሚከፈት ሲሆን የሎት 02 በቀን ከ23 / 03 /2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ይሁን እንጅ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በአል ከሆነና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆን የሚይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሰሪው መስሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ 5/አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913509999 ደውሎ መጠየቅ ይቻላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል። ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለዉ ከጨረታ ዉድድር ውጭ ያስደርጋል።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ45 ቀናት ይሆናል።
- ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመስሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል
- ለሎት 02 ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% ( ሃያ በመቶ ) መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል።
- የሎት 2 አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን ግንባታዉ በሚካሄድበት አንጭሮ ጤና ጣቢያ በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ ይጠበቅበታል።
- ለሎት 01 ጥልቅ የመስኖ የዉሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ ላይ 5 ዓመት ዓመትና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለው ሆኖ ሙሉ ማቴሪያሎችን መስራት የሚችልና ደረጃ 01 እና 2 የዉሃ ስራ ተቋራጭ መሆን ይጠበቅበታል።
- የስራ ቦታ ለሎት 01 በአብክመ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር 07 ቀበሌ ልዩ ቦታዉ /ቱሉ አዳሜ ሰንበ/
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
Summary
Kombolcha City Finance Department (Amhara) tenders deep irrigation water well drilling at Tulu Adame, Kebele 07 (Lot 1, grade 1-2 water contractors with 5+ years of experience) and building materials for Anchiro health centre (Lot 2).
