Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ
  • Address ኦሮሚያ:ኢትዮጲያ, Phone: 0335540364
  • Website
  • Deadline11 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price1000(አንድ ሺህ ብር)
  • Bid Securityብር 750,000.00 CPO ወይም ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ
  • opening dateታህሳስ 2 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Sector Construction , Irrigation Works

በአብክመ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ገንዘብ መምሪያ በደዋ ሃረዋ ወረዳ ድሬ ቀበሌ የለድሬ መዲቦ አነስተኛ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት በሙሉ ዋጋ ለማሰራት የደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የመስኖና ውሃ ግንባታ ተቋራጮችን የጋበዘበት ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር SDG 001/2019)።

በአብክመ የኦሮሞ ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SDG 001/2019 ዓ.ም

በአብክመ የኦሮሞ/ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ ለዞን ግብርና መምሪያ በ2019 ዓ.ም ከክልሉ ግብርና ቢሮ ከዘላቂ ልማት ግብ /SDG በተገኘ በጀት በደዋ ሃረዋ ወረዳ ድሬ ቀበሌ ለድሬ መዲቦ አነስተኛ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክት መስሪያ ቤታችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የግንባታ ሙሉ ዋጋ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል ።ስለሆነም

  1. ተጫራቾች በመስኖ እና ዉሃ ግንባታ ዘርፍ ደረጃ ሶስት እና ከዚያ በላይ የሆኑ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት የግብር ክሪላንስ እና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡
  2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 750,000.00(ሰባት መቶ ሃምሳ ሽህ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንተ በምርጫቸዉ በአንዱ ከዋና /original/ ከቴክኒካል ዶኩመንታቸዉ /profile/ ከያዘዉ ፖስታ ዉስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታዉን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ12/03/19 ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 20 ኛው ቀን ማለትም 01/04/19 ዓ.ም 11:30 ድረስ በኦሮሞ ብሄ/ዞን ገንዘብ መምሪያ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 ብር /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸዉን ዋና እና ቅጂ /original and copy/ ለየብቻዉ በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ታትሞ ከወጣበት ቀን 12/3/19 ጀምሮ እስከ 21 ኛው ቀን ማለትም እስከ 2/4/19 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኦሮሞ ዞን ገንዘብ /መምሪያ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ 21 ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4:01 ሰዓት ተዘግቶ 4:30 ሠዓት በግልጽ ይከፈታል። የመክፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል።
  6. የጨረታ ዉጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በመምሪያዉ ዉስጥ ማስታወቂያ የምናሳዉቅ ይሆናል።
  7. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተዉ የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  8. ዉድድሩ በድምር ዋጋ ሆኖ ዝርዝር መስፈርቶችን አሟልቶ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል።
  9. ፕሮጀክቱ የሚገኘዉ በደዋ ሃረዋ ወረዳ ድሬ ቀበሌ ዉስጥ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ከሚሴ 40 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ገባ ብሎ
  10. ግንባታዉ የሚገኝበትን ቦታ እና አጠቃላይ የሳይቱን ሁኔታ ተጫራቾች በአካል በመሄድ መጎብኘት ይኖርባቸዋል።
  11. መምሪያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነዉ።

አድራሻ - ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 325 KM ላይ ከሚሴ ከተማ እንገኛለን። ስልክ ቁጥር 0335542119 ላይ በመደወል ማንኛዉንም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

በአብክመ የኦሮሞ/ብ/ዞን/ገንዘብ መምሪያ

Summary
Oromo Nationality Zone Finance Department (Kemise, Amhara) invites grade 3 and above irrigation and water works contractors to build the Dire Medibo small-scale irrigation project in Dire kebele, Dewa Harewa woreda, under an SDG-funded agriculture budget.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender