የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ በአግራ ፕሮጀክት በጀት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ በአግራ ፕሮጀክት በጀት የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ መታደሱን የሚገልፅ ንግድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- የግዥው መጠን ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙት እቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ የቀረበው ሰነድ ማህተም በማድረግ እንዲመልሱ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ ብር በቁርጥ ሲሆን ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ/የመወዳደሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነዱና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ፖስታ እንዲሁም የፋይናንሽያል ሰነዱን በአንድ ፖስታ በመለያየት ፖስታውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 017 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ጨረታው ክፍት ሆኖ በአየር ላይ ይቆያል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 11ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4:00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 27 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ 0582266431/0583268095 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልካተቱ ሕጎች ደንቦች በግዥ መመሪያው መሠረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ
Summary
Amhara Region Bureau of Agriculture buys electronic equipment funded by the AGRA project, by open tender. Suppliers with a renewed trade licence, tax clearance and TIN may bid; VAT registration is required for purchases above 500,000 birr.
